Friday, June 14, 2024
spot_img
spot_img
spot_img
spot_img
spot_img
spot_img

ጣና ሕንፃ አስተዳደር

Share

ጣና ሕንፃ አስተዳደር

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የጣና ሕንጻ አስተዳደር በምድር ቤት፣ 1ኛ እና 2ኛ ፎቅ ላይ ያልተከራዩ ክፍሎችን ለንግድ ሱቆች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ. ለጨረታ የቀረቡ ክፍሎች የሚገኙበት               የክፍሎች ብዛትና ስፋት
1     ምድር ቤት 16 የንግድ ሱቆች ስፋታቸው ከ 2 እስከ 78.11 ካሬ ሜትር የሆነ
2     1ኛ ፎቅ 30 የንግድ ሱቆች ስፋታቸው ከ 6.50  እስከ 22.60 ካሬ ሜትር የሆነ
3     2ኛ ፎቅ 25 የንግድ ሱቆች ስፋታቸው ከ 6.25 እስከ 25.44 ካሬ ሜትር የሆነ

 

በመሆኑም ተጫራቾች ፡-

 1. በየፎቁ ለተጠቀሱት ክፍሎች የጨረታ መነሻ ዋጋ በካሬ ሜትር ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት ከተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ  ማግኘት ይችላሉ፡፡
 2. የሚከራዩትን ክፍል ጣና ህንጻ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 2-08 በአካል በመገኘት ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ድረስ ማየት ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች ለኪራይ ዋጋ ማቅረቢያ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ጣና ሕንፃ ቢሮ ቁጥር 2-08 ወይም ዳሸን ባንክ ዋናው መ/ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከፍ ብሎ በሚገኘው 6 ፎቅ በባንኩ ፋሲሊቲስ ማኔጅመንት መምሪያ ቢሮ በቅድሚያ የማይመለስ ብር 100.00 (ብር አንድ መቶ) በየትኛውም የዳሸን ባንክ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 0004012971001 ገቢ በማድረግ የከፈሉበትን ደረሰኝ በማቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች በጨረታ ሠነዱ ላይ በተያያዘው የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ III የሚከራዩበትን ዋጋ (የተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር) እና የሚከራዩትን ክፍል ለምን አገልግሎት እንደሚያውሉት በትክክል ጠቅሰው  በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሕዳር 11 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡30 ድረስ ብቻ ዳሸን ባንክ ዋናው መ/ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከፍ ብሎ በሚገኘው 6 ፎቅ በባንኩ ፋሲሊቲስ ማኔጅመንት መምሪያ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ጨረታው ሕዳር 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ተጫራቾች/ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ልደታ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው ልደታ ቁጥር 1 ዳሸን ባንክ 2ኛ ፎቅ ክፍል ቁጥር 2-.05 በይፋ ይከፈታል ፡፡
 6. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ ክፍል ብር 5,000.00(ብር አምስት ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ የተረጋገጠ ክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 7. አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ 15 ቀናት ውስጥ የኪራይ ውል መፈፀም ይኖርበታል፡፡
 8. የጨረታው አሸናፊ በተራ ቁጥር 7 መሰረት በተጠቀሰው ቀን ቀርቦ ውል ካልፈፀመ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለሕንፃ አስተዳደሩ ገቢ ይሆናል ፡፡
 9. ተከራይ ውለታ ከተፈራረመ በኋላ የሦስት ወር ኪራይ በመያዣ ወይም በመጠባበቂያ መልክ ያስይዛል፡፡
 10. የጨረታው አሸናፊ የተከራየውን ክፍል ለሌላ ሶስተኛ ወገን ማከራየት አይችልም፡፡
 11. ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 10 ድረስ ከተዘረዘሩት ነጥቦች አንዱን  አለመፈፀም ከጨረታ ለመሰረዝ ምክንያት ይሆናል፡፡
 12. ተከራይ ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 3 /ሶስት/ ቀናት ውስጥ ኪራይ ይከፍላል፡፡
 13. ባንኩ ስለኪራዩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
 • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-213 21 58 ወይም 0112 13 21 78 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ዳሸን ባንክ-ሁልጊዜም አንድ እርምጃ ቀዳሚ!

Read more