Friday, March 29, 2024
spot_img
spot_img
spot_img
spot_img

ከዚህ ቀደም ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው መመሪያ ላይ ማሻሻያ ተደረገ

Share

ከዚህ ቀደም ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው መመሪያ ላይ ማሻሻያ ማድረግ በማስፈለጉ በተሽከርካሪዎች ላይ የፍጥነት መገደቢያ መሳሪያ መግጠም ሳያስፈልጋቸው አገልግሎቱን እንዲያገኙ መወሰኑን የትራንስፓርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

“እንደሚታወቀው ወደ ሃገራችን በሚገቡ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ከሌሎች ቅደመ ሁኔታዎች በተጨማሪነት የፍጥነት መገደቢያ መሳሪያ  የማስገጠምና በተቀመጠም ስታንዳርድ መሰረት መገጠሙን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ ነበረባቸው፡፡”

ይሁንና በአተገባበሩ ላይ እየታየ ያለውን ብልሹ አሰራርና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፈተሸ እና ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችል አሰራርና አደረጃጀት ተጠናቆ ተግባራዊ እስኪደረግ ድረስ እንዲሁም የፍጥነት መገደቢያ መሳሪያው  ሊገጠምባቸው የሚገባቸው ተሸከርካሪዎች አይነትና ሌሎች ተያያዥ ችግሮችን በጥናት ምላሽ መስጠት በማስፈለጉ በፍጥነት መገደቢያ መሣሪያ አተገባበር ላይ ማሻሻያ ማደረጉን የትራንስፓርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር  በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ስለሆነም አዲስ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሃገር ውስጥ የሚያስገቡ ባለንብረቶች በማንኛውም ጊዜ መግጠም እንዳለባቸው አውቀው የግዴታ ስምምነቱን እየፈረሙና አስፈላጊ ሰነዶቻቸውን በአባሪነት እንዲያያይዙ ተደርጎ በተሽከርካሪዎች ላይ የፍጥነት መገደቢያ መሳሪያ መግጠም ሳያስፈልጋቸው አገልግሎቱን እንዲያገኙ ተወስኗል ሲል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

Read more