Friday, September 20, 2024

ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር

ጨረታ ቁጥር፡- LT/HT/HO/01/2023

የጨረታ ማስታወቂያ

ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የኩባንያው መዋቅራዊ አደረጃጀት፣የደመወዝ ስኬልና ካሪየር ዴቨሎፕመንት ጥናት እና የማማከር አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከየካቲት 27 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 – 6፡00 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 -10፡00 ድረስ “ሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ” ደብረዘይት መንገድ ጠብመንጃ ያዥ ባንክ ፊት ለፊት ከበእምነት ምግብ ቤት ጎን በሚገኘው ቤተሳይዳ ሕንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ በመክፈል እና ከተጠየቀው የአገልግሎት ግዥ ጋር ተያያዥነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የሚያቀርቡት፡-
አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ፤
አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም፣
ሁሉም (ዋናው ና ቅጂዉ) በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በሰም የታሸገ መሆን አለበት፡፡
በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል፤ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፤ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች የኩባንያው መዋቅራዊ አደረጃጀት፣የደመወዝ ስኬልና ካሪየር ዴቨሎፕመንት ጥናት እና የማማከር አገልግሎት የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ለእያንዳንዱ ሎት) ብር 20,000.00 /ሃያ ሺ ብር/ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /C.P.O/ ለሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን እስከ መጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም፣ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 306 ሲሆን፣ የጨረታው መክፈቻ ቀን መጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 303 የሚከፈት ይሆናል::
ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0114-653711 ፋክስ ቁጥር 0114-663649 መጠቀም ይችላሉ፡፡
ህዳሴ ቴሌኮም አ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ሕዳሴ ቴሌኮም
አክሲዮን ማህበር

Related Stories