Saturday, June 15, 2024
spot_img
spot_img
spot_img
spot_img
spot_img
spot_img

የስብሰባ ጥሪ

Share

ለንስር ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ. ባለአክስዮኖች በሙሉ

የንስር ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አክሲዮን ማህበር ባለአክሲዮኖች 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ቅዳሜ፤ ህዳር 01 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ በስካይላይት ሆቴል ስለሚካሄድ የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክስዮኖች የሆናችሁ በሙሉ በእዚህ ስብሰባ ላይ እንድትገኙላቸው የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥሪያቸውን በአክብሮት ያስተላልፋሉ፡፡

የአክስዮን ማህበሩ ስም                                                      ንስር ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ.

የአክስዮን ማህበሩ ዓይነት                                                   በአነስተኛ የፋይናንስ ሥራ ላይ የተሰማራ

የአክስዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ                                      ብር 372,447,000.00

የአክስዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር                                           MT/AA/3/0026952/2006

የአክስዮን ማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ                                 አዲስ አበባ፤ ቦሌ ክ/ከ ፤ ወረዳ 03፤ የቤት ቁ.084

የ10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

 1. ቆጣሪዎችን መሰየም፤
 2. ጉባዔ መሟላቱን ማረጋገጥ፤
 • አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል እና የአክሲዮኖችን ግዢ እና ዝውውሮችን ማጽደቅ፤
 • የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርትን ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ ፤
 • የውጭ ኦዲተሮች ዓመታዊ ሪፖርትን ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
 • እ.እ.አ በ2022/23 በጀት ዓመት የትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
 • ለቀጣዮቹ 3(ሶስት) ዓመታት ማህበሩን የሚያስተዳድሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን መሾም፤
 • የጉባዔውን ቃለጉባዔ በንባብ ማሰማትና ማጽደቅ፤

ማሳሰቢያ፡-

 • ማንኛውም ባለአክሲዮን በስብሰባው ላይ ለመገኘት ማንነቱን እና ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
 • ውል ለማዋዋል ህጋዊ ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠና በስብሰባ ላይ ለመካፈል እና ድምፅ ለመስጠት የሚያስችል ውክልና ያለው የባለአክሲዮን ተወካይ የውክልና ሥልጣን ማስረጃውን ዋናውንና ኮፒውን ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
 • በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ከስብሰባው 3 /ሦስት/ የሥራ ቀናት በፊት ቦሌ ሩዋንዳ አከባቢ በሚገኘው የማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የማህበሩ የአክሲዮን ክፍል በመቅረብ የውክልና መስጫ ቅፅ መሙላት ይችላሉ፡፡
 • ባለአክሲዮኖች በስልክ ቁጥር 0115 622225/ 0115 500700/01 በመደወል ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

የንስር ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ

Read more