Thursday, May 9, 2024
spot_img
spot_imgspot_imgspot_imgspot_img
spot_img
spot_img

የባለአክሲዮኖች 29ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ጥሪ2 9ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ

Share

  1. በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አንቀፅ 366(1) 367(1) 393 እና 394 መሠረት የሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች 29ኛ ዓመታዊመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ጥቅምት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል:: በመሆኑምባለአክሲዮኖች በእለቱ በጉባዔው ላይ እንድትገኙ የኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡የጉባዔው አጀንዳዎች
  2. የ29ኛው ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
    1.1 የጉባኤውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፤
    1.2 አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበልና የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅ፤
    1.3 የዳይሬክተሮች ቦርድን እ.ኤ.አ የ2022/2023 ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ፤
    1.4 የውጪ ኦዲተሮችን እ.ኤ.አ የ2022/2023 የሒሣብ ዘመን ሪፖርት ማዳመጥ፤
    1.5 በተራ ቁጥር 1.3 እና 1.4 ሥር በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
    1.6 እ.ኤ.አ ለ2022/2023 የሒሣብ ዘመን የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈል ላይ በሚቀርበው የውሣኔ ሐሳብ ላይ
    ተወያይቶ መወሰን፤
    1.7 በጎደሉ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምትክ የተተኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ስለማሳወቅ፤
    1.8 እ.ኤ.አ የ2022/2023 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ዓመታዊ የሥራ ዋጋ እና እ.ኤ.አ የ2023/2024 በጀት
    ዓመት ወርሃዊ አበል ክፍያ መወሰን፤
    1.9 የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ማካሔድና ወርሃዊ አበላቸውን መወሰን፡፡
    ማሳሰቢያ፡-
  3. በስብሰባው ላይ ለመገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ሕጋዊ ውክልና በመስጠት ወይም በኩባንያው አማካኝነት የተዘጋጀውን
    የውክልና ቅፅ ከስብሰባው ቀን አስቀድሞ በመሙላት ተወካይ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በማቅረብ የስብሰባው
    ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠትም የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
  4. ባለአክስዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ወደ ስብሰባው ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ ፓስፖርት
    ወይም የቀበሌ መታወቂያ ዋናውንና ኮፒ ይዘው መገኘት አለባቸው፡፡ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የውጭ አገር ዜግነት
    ያላቸው ባለአክስዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚያረጋግጥ የቢጫ ካርድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
    በዳይሬክተሮች ቦርድ ትዕዛዝ
    አድራሻ፡-
    አ/አ ፣ አራዳ ክ/ከ ፣ ወረዳ 02፣ የቤት ቁጥር 220፣
    ፓስታ ሣ.ቁጥር 1156
    የንግድ ምዝገባ ቁጥር፣MT/AA/3/0052572/2014
    ካፒታል፡ 1,500,000,000.00

Read more