Friday, July 12, 2024
spot_img
spot_img
spot_img
spot_img
spot_img
spot_img

የስብሰባ ጥሪለአሐዱ፡ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች በሙሉ

Share

የአሐዱ፡ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 2ኛ(ሁለተኛ) መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ኅዳር 22 ቀን
2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ስለሚያካሒድ የባንኩ
ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀን፤ሰዓት እና ቦታ በጉባዔው ላይ
እንዲገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የአክሲዮን ማኅበሩ ስም አሐዱ፡ባንክ አ.ማ.
የአክሲዮን ማኅበሩ ዓይነት የባንክ ሥራ ላይ የተሰማራ የአክሲዮን ማኅበር
የአክሲዮን ማኅበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ 671,561,500.00
የአክሲዮን ማኅበሩ የምዝገባ ቁጥ ር MT/AA/3/0052593/2014
የአክሲዮን ማኅበሩ ዋና መሥሪያ ቤት አድራሻ አዲስ አበባ፣ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 08፣የቤት
ቁጥር አዲስ

የ2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፡-
1. የጉባዔውን ድምፅ ቆጣሪዎች መሰየም

2. ምልዓተ ጉባዔው መሟላቱን ማረጋገጥ

3. የጉባዔውን አጀንዳ ማጽደቅ
4. በበጀት ዓመቱ የተፈጸሙ የአክስዮን ዝውውርን
ተቀብሎ ማጽደቅ
5. በፊርማ ጉባዔ ያልተገኙ ባለአክሲዮኖችን በተመለከተ
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አቅጣጫ መሰረት
የተፈጸመን ሂደት ማጽደቅ
6. እኤአ የ2022/23 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ
ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ
7. እኤአ የ2022/23 የውጭ ኦዲተር ሪፖርት ማዳመጥ

8. የውጭ ኦዲተርን መሾምና ክፍያ ማጽደቅ
9. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ዓመታዊ የሥራ ዋጋ
እና ወርሀዊ አበልን መወሰን
10. የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ እና ጥቆማ አሠራር
ደንብ ሰነድን ተወያይቶ ማጽደቅ
11. የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባላትን
መምረጥ
12. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ምርጫ ማከናወን
13. የጉባዔውን ቃለ ጉባዔ ተወያይቶ ማጽደቅ

ማሳሰቢያ

ባለአክሲዮኖች በጉባዔው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ከሆነ ከመስቀል
ዓደባባይ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ፍላሚንጎ ሬስቶራንት ፊትለፊት በሚገኘው
ሰንሻይን ሕንጻ 4ኛ ፎቅ የባንኩ አክሲዮን ክፍል ወይም በባንኩ ቅርንጫፎች
ከጉባዔው ሦስት ቀን በፊት በአካል በመቅረብ የውክልና ቅፅ መሙላት የሚችሉ
መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት/ቅርንጫፎች ቀርባችሁ ውክልና የምትሰጡም ሆነ
በጉባዔው በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖች ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ
መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ይዛችሁ መቅረብ አለባችሁ፡፡
በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ ሕጋዊ ውክልና ይዛችሁ የምትቀርቡ ተወካዮች
የውክልና ሰነዱን ዋና እና ኮፒ እንዲሁም የወካያችሁን ማንነት የሚገልጽ የታደሰ
መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ
አሐዱ፡ባንክ አ.ማ.Read more