Saturday, July 27, 2024
spot_img
spot_img
spot_img
spot_img
spot_img
spot_img

አክሲዮኖችን[MU1]  በጨረታ ለመሸጥ የወጣ ማስታወቂያ

Share

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በቁጥር ፋኢሱ/ባሱዳ/888/23 በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ከአምስት ባለአክሲዮኖች የተረከባቸውን በቁጥር 94,341 የሆኑ አክሲዮኖች የአንዱ አክሲዮን ዋጋ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) ሆኖ ጠቅላላ ዋጋቸው ብር 94,341,000.00 የሚያወጡ አክሲዮኖችን ለአንድ አክሲዮን የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 1,200.00 (አንድ ሺህ ሁለት መቶ) ሆኖ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መሥፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን አክሲዮኖች በከፊልም ሆነ በሙሉ መግዛት ይችላሉ፡፡

  1. የባንኩ ባለአክሲዮኖችና ሌሎች ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡ 
  2. የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ግለሰቦች ወይም ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያ ዜግነት ባላቸው ወይም የውጭ አገር ዜግነት ባለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ባለአክሲዮኖች የተያዙ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ የተመለከተውን በመሙላት ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ አገር ዜጋ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ የወረዳ መታወቂያ፤ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ወይም ሌላ ዜግነትን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፤ ወይም ተጫራቾች ድርጅቶች ከሆኑ የድርጅቱ ባለአክሲዮኖች በሙሉ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ አገር ዜጋ ባለአክሲዮን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የመመሥረቻ ጽሑፍ ወይም ሌላ በሕግ ተቀባይነት ያለው ማስረጃ እንዲሁም ድርጅቱ ህጋዊ ሰውነት ያገኘበት ከሚመለከተው ተቋም የተሰጠ የዋና ምዝገባ ወረቀት ኮፒዎች ከዋጋ ማቅረቢያው ቅፅ ጋር በአባሪነት አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የተጫራቹን ዜግነት የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያላያያዘና በዚህ ማስታወቂያ ተራ ቁጥር 2 የተገለፀውን መስፈርት የማያሟላ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  5. ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ተጫራቾች አክሲዮን ለመግዛት ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ ¼ኛ በማስላት በኢትዮጵያ ብር ገንዘቡን በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ አዘጋጅተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. አንድ ተጫራች ሁለት ጊዜ መጫረት አይችልም፡፡
  7. በጨረታው ተሳትፈው አሸናፊ የሆኑ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ወይም የውጭ አገር ዜግነት ባላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ባለአክሲዮኖች የተያዘ ድርጅት ለተጫረቱበት ጠቅላላ አክሲዮን ግዥ ክፍያውን ሙሉ በሙሉ የሚፈጽሙት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተቀባይነት ባለው የውጭ ምንዛሬ ነው፡፡
  8. ተጫራቾች ሌሎች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  9. ተጫራቾች በጨረታው ለመግዛት የሚችሉት አነስተኛ የአክሲዮን ብዛት በቁጥር 250 ሲሆን፤ ከተገለፀው መጠን በታች ለመግዛት የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  10. ለአንድ አክሲዮን ከብር 1,200.00 (አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር) በታች ሆኖ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  11. በጨረታው አሸናፊ የሚሆኑ ተጫራቾች ከዚህ ቀደም በባንኩ ካላቸው የአክሲዮን ድርሻ ጋር ተደምሮ የአክሲዮን ድርሻቸው ተፅዕኖ ፈጣሪ (Influential) ባለአክሲዮን የሚያደርጋቸው ከሆነ አክሲዮኑ በስማቸው ከመተላለፉ አስቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ፈቃድ ይጠብቃሉ፡፡ የጨረታ አሸናፊዎች የአክሲዮን ድርሻቸው በማናቸውም ሁኔታ ከባንኩ ካፒታል 5% በላይ ማለፍ አይችልም፡፡
  12. ከላይ የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ከኅዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ታህሣስ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በሥራ ሰዓት ለገሐር በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት፣ 8ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 8 የአክሲዮን እና ኢንቨስትመንት ክፍል ቀርበው በመውሰድ የሞሉትን ፎርም በተ.ቁ. 3 እና 5 ላይ የተመለከቱትን ሰነዶች አባሪ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  13. ጨረታው ታህሣስ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የሚመለከታቸው ታዛቢዎች በተገኙበት ለገሐር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ ህንፃ 12ኛ ፎቅ ላይ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡  
  14. አክሲዮኖቹ የሚሸጡት የተሻለ ዋጋ ላቀረቡ ተጫራቾች ሲሆን፤ የጨረታ አሸናፊዎች በአሸነፉት የአክሲዮን ብዛት ልክ እንዳቀረቡት የተሻለ ዋጋ በቅደም ተከተል ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡ የተሻለ ዋጋ ያቀረቡ የጨረታ አሸናፊዎች የተጫረቱበት የአክሲዮን ብዛት ከተሰጣቸው በኋላ ሌሎች ባቀረቡት የጨረታ ዋጋ ምክንያት የቅድሚያ መብት ያላገኙ ተጫራቾች የተጫረቱበትን የአክሲዮኖች ብዛት ያላገኙ ቢሆንም እንኳን የተረፉትን አክሲዮኖች ባቀረቡት ዋጋ የመግዛት ግዴታ አለባቸው፡፡
  15. አሸናፊ መሆኑ የተገለጸለት ተጫራች ወዲያዉኑ በተራ ቁጥር 3 የተገለፁትን ሰነዶች ዋና ቅጂ በማቅረብ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ውጤቱ በተገለጸለት በአምስት /5/ ቀን ውስጥ ለባንኩ ገቢ ያደርጋል፡፡ በተገለፀው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ገቢ ያላደረገ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
  16. የጨረታው ውጤት እንደታወቀ በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
  17. በጨረታው ሂደት አግባብነት ያላቸው የኢትዮጵያ ሕጎች እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወጡ መመሪያዎችና ደንቦች ተፈጻሚነት አላቸው፡፡
  18. ባንኩ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 251-11-552 63 14 መደወል ይችላሉ፡፡


 [MU1]

Read more