Sunday, April 28, 2024
spot_img
spot_imgspot_imgspot_imgspot_img
spot_img
spot_img

ኦቪድ ቤቶች ባንክ አ.ማ (በምስረታ ላይ)

Share

በአክሲዮን ሽያጭ ላይ

ኦቪድ ቤቶች ባንክ አ.ማ (በምስረታ ላይ) በኢትዮጵያ የንግድ ህግ አንቀጽ 245፣በባንክ ስራ አዋጅ ቁጥር 592/2000 እና የባንክ ስራ አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 1159/2011 መሰረት የአክስዮን ማሕበር ሆኖ በባለአክሲዎኖች ለመመስረት እና የአክስዮን ሽያጭ ለማከናወን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባገኘው ፈቃድ መሰረት የአክሲዮን ሽያጩን አስጀምሯል።

የኦቪድ ቤቶች ባንክ አ.ማ (በምስረታ ላይ) አደራጆች የባንኩ መስራች ባለአክስዮን መሆን ለሚፈልጉ አክሲዮን ገዥዎች በኢትዮጵያ ንግድ ህግ አንቀጽ 259 መሰረት በምስረታ ላይ የሚገኝ መሆኑን እየገለጽን የአክሲዮን ሽያጩን ለመፈጸም ያስቸል ዘንድ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተፈቀደልን መሰረት በተለያዩ የንግድ ባንኮች ዝግ ሂሳብ (ለዋና አክሲዮን ግዥ ) እና ተንቀሳቃሽ ሂሳብ (ለኣገልግሎት ክፍያ ) ተከፍቶ ሽያጩን በማከናወን ላይ ይገኛል።

ስለሆነም አደራጆች ባንኩን የፋይናንስ አግልግሎችን አካታች እና ተደራሽ በማድረግ እንዲሁም ሀብት ከማህበረሰቡ በማሰባሰብ  በዋናነት ለቤቶች ግዥ፣ ግንባታ፣ እድሳት እና ማሻሻያ ብድር በማቅረብ የዜጎችን የመኖሪያ ቤት እጥረት በመቅረፍ ረገድ የበኩሉን አሰተዋጽኦ በማድረግ ለባለአክሲዮኖችም ጠቀም ያለና አስተማማኝ የሆነ ትርፍ ተካፋይ እንዲሆኑ ለማድረግ አስቦ እየስራ መሆኑን እየገለጥን ማህበረሰባችን አክስዮን እንዲገዛ  በታላቅ ትህትና እና አክብሮት እንጋብዛለን።

የሚሸጠዉ አክስዮን አይነት፣ ብዛት፣ ዋጋ እና ሽያጭ

  1. የባንኩን አክስዮኖች እኩል ዋጋ ያላቸው አንድ አይነት እና ተራ አክስዮኖች ናቸው።
  2. ለሽያጭ የቀረቡ አክስዮኖች ብዛት 20,000,000 (ሃያ ሚሊዮን) ነው።
  3. የአንድ አክስዮን ዋጋ ብር 1000 (አንድ ሺ ብር) ነው።
  4. አንድ ባለአክስዮን ሊገዛው የሚገባው ዝቅተኛ የአክስዮን ብዛት 200 (ሁለት መቶ) ወይም በብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ) ዋጋ ያላቸው አክስዮኖችን ነው።
  5. አንድ ባለአክስዮን መግዛት የሚችለው ከፍተኛ የአክስዮን ብዛት 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን) ወይም በብር 1,000,000,000.00 (አንድ ቢሊዮን) ዋጋ ያላቸው አክስዮኖችን ነው።
  6. አንድ ባለአክስዮን ከላይ በተራ ቁጥር 4 እና 5 በተገለጠው መሰረት ለመግዛት ከፈረመው አክስዮን ውስጥ ቢያንስ 25% (ሃያ አምስት በመቶ) ሲፈርም መክፈል ያለበት ሲሆን ቀሪውን በአንድ ጊዜ ወይም በተለያየ ጊዜ ከምስረታው ጉባኤ በኋላ ባሉት ሁለት ዓመታት  ጊዜ ውስጥ መከፈል ይኖርበታል።
  7. አንድ ባለአክስዮን ለመግዛት ከፈረመበት አክስዮን መጠን ላይ 5% (አምስት በመቶ) የአገልግሎት ክፍያ መክፈል ይኖርበታል።

ማሳሰቢያ፡፟የአክስዮን ሽያጩ የሚከናወነው ለኢትዮጵያዊያን ዜጎች በብር  ሲሆን ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለሆኑ የውጭ አገር ዜግነት ላላቸው አክሲዮን ገዥዎች ግዥውን መፈፀም የሚችሉት በብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/73/2020 መሰረት ተቀባይነት ባላቸው  የውጭ  ሀገራት ገንዘቦች ብቻ ይሆናል።

         አደራጅ አባላት                                                                                                                                  

  1. ዶ/ር ይትባረክ ታከለ ……… ሰብሳቢ                           
  2.  አቶ አብይ ግርማ …………. ም/ሰብሳቢ                
  3. አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ………. አባል                      
  4. አቶ ያሬድ ብርሃኔ …………. አባል                        
  5. ወ/ሪት ስህን ለገሰ ………….. አባል         
  6. ወ/ሮ ጌጤነሽ ታደሰ…………….ኣባል እና ፀሃፊ                                            

የአክሲዮን ሽያጭ የሚከናወንባቸው ባንኮች ዝርዝር

1. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ                             6. ዘመን ባንክ አ.ማ

2. አቢሲኒያ ባንክ አ.ማ                                7. ወጋገን ባንክ አ.ማ

3. ዳሽን ባንክ አ.ማ                                     8. ህብረት ባንክ አ.ማ

4. ፀሃይ ባንክ አ.ማ                                     9. ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ አማ

5. አማራ ባንክ አ.ማ

ለበለጠ መረጃ አትላስ አካባቢ ፕላቲኒየም ፕላዛ 4ኛ ፎቅ የሚገኘዉን የባንኩን የፕሮጀክት ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0904151411 በመደወል ማናገር የምትችሉ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን፡፡

Read more