Thursday, March 28, 2024
spot_img
spot_img
spot_img
spot_img

ቴክኖ በአለም አቀፍ ገበያ ላይ ለመስፋፋት የሚያደርገውን ጥረት ለማጠናከር እንዲረዳው ታዋቂውን የሆሊዉድ ተዋናኝ ክሪስ ኢቫንስን የድርጅቱ የንግድ አምባሳደር አድርጎ ሾሞታል

Share

  • ከክሪስ ኢቫንስ ጋር የተደረገው ስምምነት TECNO በይበልጥ እያደጉ ባሉ አገራት ገበያዎች ላይ መግባት እንዲችል እና እንዲሁም መሪ ለመሆን የሚያስችለውን ስትራቴጂ አጠናክሮታል::

በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆነው ተወዳጁ የስማርት ስልክ አምራች ቴክኖ የማድረግ አቅሙን ባሳየ መልኩ በሆሊውድ ዝነኞች ዝርዝር ውስጥ ቀዳሚ ስፍራ ውስጥ የሚገኘውን ዝነኛውን ክሪስ ኢቫንስን የድርጅቱ የንግድ አምባሳዶር አርጎ አስፈርሞታል::

እስከ ዛሬ ከተደረጉት ሁኔታ ቀያሪ ውሳኔዎች ሁሉ የሚበልጠው ይህ አስደናቂ እርምጃ በማርቭልም ሆነ በቴክኖ ደጋፊዎች መካከል በመላው ዓለም  መነጋገሪያ መሆን ችሉዋል። ይህ የስምምነት ፊርማ TECNO ይበልጥ በአለም አቀፍ ደረጃ ታዳጊ አገራት ገበያዎች ላይ ለመግባት የሚያደርገውን ጥረት ለማሳካት እንዲሁም በእነዚህ አካባቢዎች መሪ ለመሆን የሚያስችለውን ስትራቴጂ አጠናክሮታል::

TECNO የንግድ ምልክቱ በዓለም መድረክ ላይ እያደገ ሲሄድ፣ ከዋና ዋናዎቹ የንግድ አምራቾች ጋር  ጋር እየተፎካከረ ይገኛል:: በአሁኑ ጊዜ ፤ እነዚህ ተፎካካሪ የንግድ ድርጅቶች ቁጭ ብለው ይህን የቴክኖን የጎላ  እንቅስቃሴ እንደሚያስተውሉ ምንም ጥርጥር የለውም።

በማርቨል ዩኒቨርስ ተከታታይ ፊልሞች ውስጥ ካፒቴን አሜሪካን በመሆን ሲተውን የሚታወቀው ዝነኛው ክሪስ ኢቫንስ ከTECNO ጋር ሊያመሳስሉት የሚችሉ ብዙ ባህሪያት ያሉት ሲሆን በተለይም እያንዳንዱን ችግር የመወጣት እና የመጨረሻ ስኬት ለማግኘትያለው ታታሪነት ከቴክኖ ጋር አንድ ያደርጋቸዋል::

የሁለትዮሽ ትብብሩ ዝነኛው የቴክኖን “Stop At Nothing” የሚለውን ፍልስፍና ለሰዎች በማንፀባረቅ እና ሰዎች በህይዎት የሚፈልጉዋችውን ነገሮች ለማሳካት ከሚያረጉዋቸው ሩጫዎች እንዳይቆጠቡ እና ሁልግዜም በልባቸው የወጣትነት መንፈስ ይዘው እንዲንቀሳቀሱ እንዲያበረታታቸው የሚያደርግ ነው:: በክሪስ ኢቫንስ የተንጸባረቀው ከሆሊውድ የመነጨው ዓለም አቀፋዊነት ስብዕናው እና የሚያምር የፋሽን ተከታይነትባሕርይ፣ የቴክኖ ምርት ንድፍና ባሕርያትን ያንጸባርቃል፤ ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚያምር፣ ጠንካራ፣ ዘላቂና የማያቋርጥ አቅኚነት ያለው እና የሰውን መንፈስ የሚስብ ነው::

ከቅርብ 2 ዓመታት ወዲህ TECNO የቴክኖሎጂ ፈጠራውን በማጠናከር በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ አንዳንድ አዎንታዊ ውጤቶችን አግኝቷል:: በጥቂቱ ለመጥቀስ ፣ በአለም አቀፍ ደረጃ ከተለያዩ የላቀ አዕምሮ ካላቸው ሰዎች ጋር በመወዳደር በሞባይል ፎቶግራፊ በ 2020 ዓ.ም. በተደረገው Look In Person (LIP) ውድድር በኮምፒውተር እይታ እና የንድፍ ዕውቅና አምስተኛ ደረጃን ያገኘ ሲሆን በ Dark Complexion Portrait Segmentation እንዲሁ ዕውቅናን ተችሮታል:: ከዚህ በተረፈ በዓለም አቀፍ ደረጃ የቴክኖሎጂ ምርቶች ላይ የገበያ ጥናት በማድረግ ታዋቂ የሆነው Counterpoint research institute ቴክኖን በAI( artificial Intelligence) በታገዘው የሞባይል ፎቶግራፊ አና ቪዲዮ ግራፊ አማራጩ አዲስ እምርታን ያመጣ ስልክ ሲል እውቅና ሰጥቶታል:: እንዲሁም በGuinness World Records 2020 በታውቂው ምርቱ CAMON በተነሱት ፎቶዎች the largest flip book shot በሚል መደብ ስልኩ የdistinctions ደረጃን ተሰጥቶታል::

እንዲሁም በ 2020 በበርሊን በተካሄደው የ IFA(Internationale Funkausstellung Berlin) ውድድር በ “Camera Technology Innovation”  ዘርፍ የወርቅ ሽልማት አግኝቱዋል::

በአለም አቀፍ ደረጃ  እየጨመረየ ያለው የቴክኖ የገበያ ድርሻ ቴክኖ በአለም አቀፍ ገበያዎች ላይ እያሳረፈ ላለው አሻራ ማሳያ ይሆናል:: ምንም እንኩዋን ለብዙ የስልክ አምራቾች 2020 አስቸጋሪ አመት ቢሆንም ቴክኖ ግን በስኬት ለማጠናቀቅ ችሉዋል።እንደ አለማቀፉ የገበያ መረጃ ኩባንያ IDC ሪፖርት መሰረት የTECNO የሽያጭ መጠን ከ 25 ሚሊዮን ዩኒት በላይ ሲሆን ይህም የ 45% ጭማሪ አሳይቱዋል::  በገንዘብ ሲተመን ገቢው ከ 15 ቢሊዮን dolar በላይ ሲሆን ካለፈው አመት የ38% ጭማሪ አሳይቱዋል:: እንዲሁም በህንድ በ2020 ዓ.ም. የTECNO ስማርት ስልክ ሽያጭ ከ 5 ሚሊዮን ዩኒት በላይ በመሆን ከ200% በላይ ጭማሬ አሳይቱዋል:: ይህም ደግሞ የራሱን የሽያጭ እድገት ሪኮርድ መስበር አስችሎታል:: በነዚህ መሰል እምርታዎች ከቀጠለ መጪውን የቴክኖ ምርት አዲስ ከፍታላይ ለመውጣት የሚያግደው ምንም ነገር ያለ አይመስልም:: እንደ Counterpoint ሪፖርት መሰረት መጭው ጊዜ ለTECNO ታላቅ እምርታ የሚመዘገብበት ተስፋን ይዟል።

ባለፉት ግዜያቶች ውስጥ ቴክኖ የማሰብ ችሎታ ያላቸው የተራቀቁ መተግበሪያዎችን እና ስልክ ላይ የሚገጠሙ ተቀጽላ መሳሪያዎችን ለማዘመን በምርምር ረገድ የሚያወጣውን ኢንቨስትመንት እና ንድፍ ሃሳብ ለማጠናከር እንዲሁም ሃርድዌር እና ሶፍትዌርን የሚያቀናጅ የማሰብ ችሎታ ያለው ሥነ ምህዳር ለመገንባት ቃል ገብቷል። በ 2020 ቴክኖ በምርምር ረገድ ያወጣው ኢንቨስትመንት በዓመት ውስጥ በ 30% ገደማ ጨምሯል:: ይህ ቴክኖ በምርምር የሚያወጣው ኢንቨስትመንት የቴክኖን የገበያ ድርሻ ከፍ እንዲል ማገዙን ከቀጠለ ቴክኖ ድጋፉን ይቀጥላል ።

በአሁኑ ጊዜ ቴክኖ ከታዋቂው ክሪስ ኢቫንስ ጋር እና ከአራቱ ታዋቂ ስም ካተርፋቸው ምርቶቹ ጋር በመሆን ከሌሎች ጎልቶ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ እንደ እንጸባራቂ ኮከብ ጎልቶ እንዲታይ አርጎታል። በክሪስ ኢቫንስ የተደገፈው በጣም ተወዳጅ የሆነው የ TECNO CAMON ተከታታይ ስልክ አዲሱን CAMON 17ን በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ገበያ ላይ አውጥቶ መነጋገሪያ ለመሆን ተዘጋጅቱዋል:: የTECNO CAMON ተከታታይ ስልክ በግሩም የፎቶግራፍ የማንሳት አቅሙ የታወቀ ሲሆን በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን በኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ብዙ እውቅናንም አግኝቱዋል::

ኢንዱስትሪው ከዚህ በመቀጠል ዝነኛው ኢቫንስ የት እንደሚታይ ለማወቅ እንደሚገመት ምንም ጥርጥር የለውም ። ክሪስ ኢቫንስ እና TECNO አንድ ላይ ምን አይነት አዲስ ከፍታ ላይ ይወጡ ይሆን?

Read more