በድሬዳዋ ኤርፖርት የጦር መሳሪያ ፍንዳታ ተከሰተ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሐሰት መሆኑ ተገለፀ።

0
532

በድሬዳዋ ኤርፖርት የጦር መሳሪያ ፍንዳታ ተከሰተ ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተላለፈው መረጃ ሐሰት መሆኑን
የድሬዳዋ ሲቪል አቪየሺን ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ሽመልስ ገልጸዋል።

ፍንዳታው የተከሰተው በትላንትናው ዕለት ከቀኑ 10 ሰዓት ከ50 ደቂቃ የአውሮፕላኑን አቅጣጫና የርቀት መለኪያ፣ የኃይል መቆጣጠሪያና የመገናኛ መሳሪያ በኤሌክትሪክ ኃይል መጨመር በተከሰተ ቃጠሎና ፍንዳታ የኃይል መቆጣጠሪያ ስርዓቱ ላይ አደጋ መድረሱን ገልፀዋል፡፡

ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳልተከሰተና ኤርፖርቱ የተለመደ በረራውን እያካሄደ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡